አባይ ሚድያ(ጥቅምት 2፣2012) ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ ከተማ ፍልውሃ አካባቢ 2 የፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የፌደራል ፖሊስ ኮምንኬሽን ተናግሯል። 4 አባላት መቁሰላቸውንም ተሰምቷል።
የኮሚንኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ጄላን አባሎቹ በአካባቢው የሚኖሩበት ቦታ አለ በጥበቃም የተሰየሙ ነበሩ የሚል መልስ ሰጥተዋል።
ምክንያቱም ምን እንደሆነ የተጠየቁት የስራ ሀላፊ የአንድ አባል ቀልድ መሳይ ብሽሽቅ እንደሆነ ተናግረዋል። በተጀመረውም ብሽሽቅ አንደኛው አባል 2 ጓደኞቹን በእጁ በያዘው መሳሪያ ተኩሶ መግደሉን የፌደራል ፖሊስ ተናግረዋል።
ህይወት ያጠፋው አባልም እንደቆሰለ እና ጉዳዩ በምርመራ እንደሆነ ታውቋል።