አባይ ሚዲያ(ጥቅምት 3፣2012) ከሰኔ 15 ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በማረፊያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት የአማራ ክልል ከፍተኛ የጸጥታ ሃላፊዎች በዋስ እንደሊቀቁ ተወስኗል፡፡

በዚህም ብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ እና ኮሎኔል ባምላኩ እያንዳንዳቸው በአስር ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ መወሰኑን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡