አባይ ሚዲያ ዜና – ጥቅምት 4፣ 2012

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በመዲናዋና በአማራ ክልል በተካሄደው ጥቃትና መንግስት መፈንቅለ መንግስት ነው ብሎ በሰየመው ሁነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት 59 ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተገለፀ፡፡

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ፣ የአስራት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ጋዜጠኛ ጌታቸው አምባዬን ጨምሮ 59 ዜጎች እስር ለ3 ወራት ያህል ያለምንም ፍርድ በእስር ላይ እንደሚገኙ ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ለአባይ ሚዲያ ተናግሯል፡፡

እንደ ጋዜጠኛ እስክንድር ከሆነ 59ኙም ከቅዳሜ ጀምሮ በረሃብ አድማ ላይ ይገኛሉ፡፡ለዚህም እንደምክንያት የሚያነሱት ፍርድ ቤት፣ ዐቃቤ ህግ በአጠቃላይ የፍትሕ ስርዓቱ በአግባቡ እያስተናገደን አይደለም በሚል ነው፡፡

ከ59ኙ መካከል ከጠያቂ ወይም ከቤተሰብ ጋር የሚገናኙት ሦስት ብቻ መሆናቸውን ጋዜጠኛ እስክንድር ተናግሯል፡፡