አባይ ሚዲያ ዜና – ጥቅምት 5፣ 2012

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ህገ መንግስቱ የፈቀደልንን መብት ተጠቅመን ቅስቀሳ እያደረግን ባለንበት በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለናል ሲሉ የኢህአፓ ሊቀመንበር አቶ መርሻ ዮሴፍ ለአባይ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ ቅስቀሳ እያደረግን ያለነው በተሸከርካሪዎች እና በበራሪ ወረቀቶች ሲሆን በድምጽ ማጉያ የሚቀሰቅሱ አባላት ከነ ሙሉ ቁሳቁሶቻቸው ምንነቱ ባልታወቀ ምክንያት ፖሊስ ቅስቀሳውን አስቁሞ ወደ ካራ ማራ ፖሊስ ጣቢያ ወስዶ ትዕዛዙ ከበላይ አመራሮች የተሰጠ እንደሆነ በመግለጽ እንዳሰራቸው እና ለእንግልት እንደዳረጋቸው አቶ መርሻ ይናገራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ በደርግ ዘመነ መንግስት በደረሰበት ጭቆና ከሃገር እንደወጣ እና ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ከሃገር ውጭ ቆይቶ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ሃገር ቤት መግባቱ ይታወቃል፡፡