አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 19፣2012

ሰሞኑን በአንዳንድ የአገራችን ዞኖችና ወረዳዎች በተከሰተው ችግር ምክንያት የሰው ሕይወት መጥፋት እና ንብረት ውድመት መድረሱ ይታወቃል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በጀርመን ፍራንክፈርት እሁድ ኖቬምበር 3 በሀፕዋች በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን የአለም አቀፉ ህብረተሰብ በኢትዮጵያ የጥፋት ሃይሎችን እንዲያወግዝ እንጠይቃለን የሚልና የተለያዩ መፈክሮችን ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል፡፡

በሰልፉ ላይም በጀርመን ያሉ የተለያዩ የማህበረሰብ አደረጃጀቶች የሃይማኖት ተቋማት ግለሰቦች በጋራ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የጀርመን እና አለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደሚጋበዙ ተገልጿል።