አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 19፣2012

ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ከሚገኝባቸው አንዱ ቤንሻንጉል ጉሙዝ በክልሉ እየተመረተ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ፣ ከአመራረቱ እስከ ግብይቱ በችግሮች መተብተቡ ተገልጧል፡፡

ህገወጥ ንግድ፣የጸጥታ ችግርና ኋላቀር የአመራረት ዘይቤ ተደምሮበት አፈጻጸሙን ዝቅተኛ እንዳደረገውም ይነገራል።

አምራቾቹ የተመረተውን ወርቅ በተተመነ ዋጋ ለመሸጥ ስለማይፈልጉ በተሻለ ዋጋ ለህገወጥ ነጋዴዎች ያስረክቡታል  በዚህም ህገወጥ ነጋዴዎቹ እየከበሩ፣ ህጋዊዎቹ ለኪሳራ እንደዳረጋቸው ህጋዊ አምራቾች ይናገራሉ።

እነርሱ ህገ ወጥ ንግዱ እየጎዳቸው እንደሚገኝ ፣ በተገቢው መንገድ ወርቅ ለማግኘት ተጽዕኖ ማሳደሩን፣ መንግሥትም በህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ባለመሆኑ መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚገባ ይጠቁማሉ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን የሱዳን መውጫዎች ለህገወጥ ንግዱ መንስዔ በመሆናቸው ችግሩን ለማስወገድ የተጠናከረ የቁጥጥር ሥራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡