አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 19፣2012

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን አንዱዓለም እንደተናገሩት ባለስልጣኑ በመላው አገሪቱ የሚገኙ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን የማጠናከር ተግባር ላይ እንደሚያተኩር ገልጸዋል።

የተቋቋሙ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች በአቅም ማነስና ሌሎች ችግሮች እየተንገዳገዱ ባሉበት ሁኔታ አዲስ መክፈት አስፈላጊ አለመሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ለሶስት የንግድ ሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ለመስጠት ጨረታ መውጣቱን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አስታውቋል።

እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለጻ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ቁጥር መጨመር የህብረተሰቡን መረጃ የማግኘት አማራጭ ያሰፋዋል።

የመገናኛ ብዙሃን ቁጥር እንዲጨምር ከማድረግ ጎን ለጎን ሙያን መሰረት በማድረግ የተቋቋሙለትን ዓላማ እንዲያሳኩም ለማገዝ ባለስልጣኑ አቅም የማጎልበት ተግባር እንደሚያከናውን ተናግረዋል።

ለዚህም ከኳታር መንግስት ጋር በመሆን የመገናኛ ብዙሃን ማሰልጠኛ ማዕከል ለመገንባት መታቀዱን አቶ ወንድወሰን አስታውቀዋል፡፡