አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 19፣2012

በኮሬ ብሔረሰብ እና በጉጂ ማህበረሰብ መካከል በተፈጠረው ግጭት የበርካቶች ህይወት በመጥፋቱ እና ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ተከትሎ የኮሬ ብሔረሰብ የጋሞ ባይራ ሐገር ሽማግሌዎች እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ ጠይቀዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ በኢትዮጵያ የሰላም ተምሳሌት የሆኑት የጋሞ ባይራ የሐገር ሽማግሌዎች የቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ግጭት የገቡትን ሁለቱን አካላት ከ6 ጊዜ በላይ ተመላልሶ በማወያየት እና በማደራደር ሰላም እንዲወርድ አድርገዋል፡፡

በእርቅ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ሁለቱ አካላት ዳግም ወደ ግጭት እንዲገቡ የሚቀሰቅሱ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡