አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 21፣2012

የኢትዮጵያዊያን ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ኢሃን የሀገሪቱን ወቅታዊ ጉዳይ በማስመልከት በዛሬው እለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣አሁን ባለበት ደረጃ መንግስት አለ ብሎ ለመናገር እንደሚከብድ ተናግሯል፡፡

ስርዓት አልበኝነት ሰፍኗል፤በዜጎች ላይም ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነዉ፤ይህ የሚሆነዉ ደግሞ የመከላከያና የጸጥታ አስከባሪ አካላት ባሉበት መሆኑ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ አለመቻሉን ማሳያ ነዉ ብሏል፡፡

የፓርቲዉ ሊቀ-መንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት እንዳሉት፤መንግስት ህዝቡ የሰጠዉን ተደጋጋሚ እድል በሚገባ አልተጠቀመበትም፤በተደጋጋሚ ተፈትኖ ወድቋል ብለዋል፡፡

መንግስት ለፖለቲካዉ ጉዳይ ሲል የዜጎችን ህይወት እየገበረ ሊቀጠል አይገባም ያሉት ሊቀ-መንበሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ያስፈልገዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት በተሰጠዉ ምላሽ እርምጃ የማንወስደዉ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ነዉ የተባለው ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ፡፡

የፖለቲካ ምህዳር የሚሰፋዉ ትክክለኛ አሰራርን በመከተል እንጂ በአጥፊዎች ላይ እርምጃ ባለመዉሰድ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፓርቲው በመግለጫው በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋምም ጠይቋል፡፡