አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 23፣2012

ትናንት  ማታ በመስሪያ ቤቱ አካባቢ የተሰባሰቡ ግለሰቦች ጥቃት ሊፈጽሙበት እንደነበር ተናግሯል፡፡

አዲስ አበባ በሚገኘው የባለ አደራ ምክር ቤቱ መስሪያ ቤት ስብሰባ አድርገን እንደጨረስን  ስንወጣ  አስር የሚደርሱ ወጣቶች ተሰባስበው ጥቃት ለመፈጸም ከበባ እንዳደረጉበታቸው የሚናገረው እስክንድር ከአስሩ ውስጥ ዘጠኙ ሲያመልጡ አንዱ በአካባቢው ፖሊሶች ቅጥጥር ስር እንደዋለ እና ሲጠየቅ ተማሪ እንደሆነ ቢያስረዳም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ ሲጠየቅ ምክትል ሳጅን እንደሆነ በሰጠው የእምነት ቃል እና በያዘው መታወቂያ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ጉዳዩም በፖሊስ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን የሌሎችን ዘጠኝ ሰዎች ማንነት እና ዓላማ ፖሊስ ሲደርስበት የምናሳቅቅ ይሆናል፡፡