አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 24፣2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ ወመዘክር ከአሜሪካን ኤምባሲ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ1.3 ሚሊዮን ብር በዋናው አዳራሽ ላይ የሚያደርገው እድሳት በሰኔ 2011 የተጀመረ ሲሆን በመስከረም 2012 ይጠናቀቃል ቢባልም ስራውን የያዘው ኮንትራክተር ያለ ግንባታ ዲዛይን አማካሪ የሚሰራ በመሆኑ የወንበሮቹ አቀማመጥ ለጣሪያው በጣም በመቅረባቸው ምክንያት ፈርሶ እንዲሰራ መደረጉን የኤጀንሲው ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ይኩኖአምላክ መዝገቡ ተናግረዋል፡፡

እድሳቱ በተያዘለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ በአዳራሹ መደረግ የነበረባቸው ኪነ-ጥበባዊ ፕሮግራሞችንና የመጻሕፍት ምርቃትን ማካሄድ እንዳልተቻለም ተገልጧል፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ ከኮንትራክተሮች ጋር ውይይቶችን በማድረግ እድሳቱን በጥቅምት ወር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን ለተፈጠረው ስህተት ሙሉ ለሙሉ ወጪውን ኮንትራክተሩ እንዲሸፍን ተደርጓል፡፡