አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 24፣2012

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተፈጠሩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠገን መደመር ትክክለኛ አማራጭ እንደሚሆን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አማካሪ አቶ ሌንጮ ባቲ ገልጸዋል፡፡

አቶ ሌንጮ ባቲ እንዳሉት በኢትዮጵያ የተበላሸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርአት ለማስተካከል ብቸኛው አማራጭ ፌዴራሊዝም ሲሆን መደመር ደግሞ እውነተኛ ፌዴራሊዝም እንዲመጣ የሚያደርግ አተያይ ነው።

ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በርካታ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስብራቶች ተፈጥረዋል የሚሉት አቶ ሌንጮ እነዚህን ስብራቶች ለመጠገን ደግሞ መደመር ትክክለኛ አማራጭ እንደሚሆን አመልክተዋል።

መደመር “አህዳዊነትን የሚያመጣ ነው” በሚል በአንዳንድ አካላት የሚነሳው ሃሳብም መሰረተ ቢስ መሆኑን ተናግረዋል።