አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 24፣2012

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከሰኔ 15 ክስተት ጋር በተያያዘ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር፡፡

ዛሬ በማኅበራዊ ገጹ ባወጣው መግለጫ ደግሞ ‹‹ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለሚዲያ አካላት ለመስጠት የታቀደ ጋዜጣዊ መግለጫ በሌሎች አስቸኳይ የሥራ ጉዳዩች ለሌላ ጊዜ የተላለፈ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን›› ሲል አስታውቋል።

በሌላ ጊዜ መግለጫው መቼ እንደሚሰጥ አልተመላከተም፡፡