አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 25፣2012

ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ ከዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወጣቶች ጋር የአኖሌ ሀውልትን ሲጎበኙ ባደረጉት ንግግር ለህዝቦች አብሮነት የሚጠቅመው አንዱ የሌላውን እውነታ መረዳትና መቀበል ሲችል ነው፡፡

በኦዲፒ የሚመራው መንግስት እና አጋሮቹ የቴሌቪዥን ዛቻ እና ግርግር ወደ ድሮው የሚመልሳቸው ከመሰላቸው ስህተት ነው አንደዚህ አይነት ወጣትም ጊዜም የለም ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ ለእንደዚህ አይነቱ አካሄድ እውቀቱም ብቃቱም የለም ብለዋል፡፡

ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ እንደተናገሩት በአሁን ጊዜ በአዲስ አበባ ላይና የኦሮምኛ ቋንቋን በተመለከተ ያለን ጥያቄ፣የራሳችንን መንግስት በወረቀታችን መርጠን የማግኘትና የፌደራል ስርአቱ ከእውነተኛ ኮንፌዴሬሽን የመነጨ እንዲሆን የማድረጉ መሰረታዊ ጥያቄ ባልተመለሰበት ህዝባችን ታግሶ እስከምርጫ ያድረስን ብሎ እየጠበቀ ባለበት ጊዜ ኦሮሞ መንግስቴ ነው ብሎ ያመነው ሀይል ከነፍጠኛ ጋር በዚህ መንገድ መጓዙ በጣም አሳፋሪ ነው፡፡

ብርጋዴር ጄነራሉ ህወሐትን ከስልጣን ያስወገደው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ አልተመለሰም ሲሉም አክለዋል፡፡

በኦዲፒ የሚመራው መንግስትና አጋሮቹ ጭምር የኦሮሞና ሌሎች ጭቁን ህዝቦች ወደታገሉለት መስመር እንዲመለሱ መልዕክታችን ነው ያሉ ሲሆን ይህ የምርጫ ጉዳይ ነው ካልተመለሱ በነፍጠኛ መንገድ እንዲቀጥሉ በዚህ አካሄድ የሚመጣውን ውጤት አብረን እናያለን ሲሉም ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ አክለውም ከህዝቡ ጋር መሆን ወይ ደግሞ ከነፍጠኛ ጋር መሆን ነው በዚህ ሁለት ምርጫ መሀል ክፍተት የለም ብለዋል፡፡