አባይ ሚዲያ ዜና- ጥቅምት 25፣2012

ከሰኔ 15ቱ የጀነራል ሰዕረ መኮንን ግድያ ጋር በተያያዘ በግድያው ተሳትፏል በሚል ቆስሎ የተያዘው መቶ አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ተጠርጣሪው ያለፉትን ወራት ህክምና ላይ የነበረ ሲሆን ዛሬ በአራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ የወንጀል ችሎት በዝግ ምስክርነት መስጠት ጀምሯል።

የተጠርጣሪው መቶ አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ የምስክርነት ሂደት ነገም እንደሚቀጥል ዋዜማ ዘግባለች።

መቶ አለቃ መሳፍንት በትላንትናው እለት ከሆስፒታል መውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡