አባይ ሚዲያ ዜና-ጥቅምት 25፣2012

የግብጽ፤ ደቡብ ሱዳንና ኡጋንዳ መሪዎች የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በድብቅ እየመከሩ ነው ብሎ የደቡብ ሱዳን የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

የዜና ወኪሉ አንድ የቀድሞ የኡጋንዳ የደህንነት ሰራተኛ ያደረሰውን ባለ 3 ገጽ ዶክመንት ጠቅሶ እንደዘገበው የሶስቱ ሀገራት መሪዎች አብደልፈታህ አልሲሲ፤ ዩዌሪ ሙሴቬኒና ሳልቫኪር መጠነ ሰፊ ምክክር እና ሴራ በድብቅ እየወጠኑ ነው ብሏል፡፡

ቀደም ሲል ለኡጋንዳ የውጭ ደህንነት ድርጅት ሲሰራ የነበረው የስለላ መኮንን ሀገራቱ የታላቁ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዳይጠናቀቅ ለመከላከል ሌት ከቀን እየሰሩ ናቸው ያለ ሲሆን ለዚህም በዲፕሎማሲ እና በወታደራዊ መንገዶች አማካይነት በኢትዮጵያ ላይ የበለጠ ጫና ለማሳደር ተመሳጥረዋል ይላል፡፡

ሰነዱ እንደሚያሳየው ይላል የዜና ወኪሉ  ሦስቱ አገራት ፍላጎቶቻቸውን ለማሳካት በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ውስጥ ኮርፖሬሽናቸውን እንዴት እንደሚያቀናጁ እያሴሩ ሲሆን ግብጽ ኡጋንዳን የመጀመሪያ ተባባሪ እንድትሆን የሚያደርግ ሁኔታ ተፈጥሯል ሲል ያትታል፡፡

በሰነዱ ውስጥ ኢትዮጵያ ግድቡን እንዳታጠናቅቅ ለመከላከል የታቀዱ “ከባድ ቴክኒኮች” የተካተቱ ሲሆን ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋጋት ከወሰነች ዕቅዱ ኡጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን  ግብፅን መርዳት አለባቸው የሚል ነው ተብሏል፡፡

“ኤል-ሲሲ ሁል ጊዜ የጦር መሳሪያዎችን እና ጥይቶችን ወደ ጁባን በሁለት የተለያዩ መንገዶች ያቀርባል የሚለው ጀምስ በመድኃኒት ወይም በግብርና ምርቶች መልክ ይሰጣል ወይም ኡጋንዳን እንደ ሽፋን ይጠቀማል ብሏል፡፡

ሲጠናቀቅ ከአፍሪካ አንደኛ የሀይል ማመንጫ ይሆናል የተባለው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረ ሰሞን የኢትዮጵያ መንግስት የደቡብ ሱዳንን አመጽ ግብፅ እና ኤርትራ ደግፈዋል ሲል እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ጄምስ ሞይስ በኡጋንዳ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ምስጢሮችን ያጋለጠ ሲሆን ከዚህ በፊት እ.ኤ.አ. በሐምሌ ወር 2013 ባወጣው ሰነድ ውስጥ የሳልቫኪርንና እና የሙሴቬኒን ዕቅድ ማጋላጡ ይታወሳል፡፡