አባይ ሚዲያ ዜና-ህዳር 9፣2012

አክቲቪስትና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ጀዋር መሀመድ በዚህ አመት በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ከገለጸ በኋላ ከቀናት በፊት ለተለያዩ ፖለቲካዊ ውይይቶችና ቅስቀሳዎች ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዞ ከደጋፊዎቹ ጋር በተገናኘባቸው መድረኮች ላይ የተለያዩ ተቃውሞዎችን እያስተናገደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ከሁለት ቀን በፊት በአሜሪካ ሲያትል አቶ ጀዋር ሙሀመድን የሚያወግዙ ኢትዮጵያዊያን ነዋሪዎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የፊታችን እሁድ በቶሮንቶ በአቶ ጀዋር ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል፡፡

በተጨማሪም አቶ ጀዋር መሀመድ ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማካሄድ ባቀደበት ሃሙስ በላስ ቬጋስ፣ አርብ በዴንቨር፣ ቅዳሜ በዲሲ እንዲሁም እሁድ በቶሮንቶ የተቃውሞ ሰልፍ መጠራቱን የሰልፉ አስተባበሪዎች ገልጸዋል፡፡