አባይ ሚዲያ ዜና-ህዳር 12፣2012

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው በአገሪቱ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ነቢያት በዚህ ጊዜ እንዳሉት መንግስት በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊያንን ፍርድ ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ተናግረዋል።

ፍርዱ ተፈጻሚ እንዳይሆን ወይም ኢትዮጵያዊያኑ በህይወት መቆየት የሚችሉበትን አሰራር ለመዘርጋት ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጋር ከመነጋገር አልፎ ጠበቃ እንደቀጠረላቸው ገልጸዋል።