አባይ ሚዲያ ዜና- ህዳር 17፣2012

ከአሁን በፊት በኢትዮጵያ ሚዲያዎች ላይ የሚታወቀው አንጋፋው ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ በአሁኑ ሰዓት በዘመኑ የማይጠበቁ ክስተቶች ብቅ እያሉ ነው ሲል ንግግሩን በመጀመር በአንድ ሰፈር እድርተኛ የነበረ ማህበረሰብ ዘር እየቆጠረ እርስ በእርስ የሚጨራረስበት ድግስ እየተሰናዳለት እንደሆነ በመግለጽ የአያትና የቅድመ አያት ታሪክ እየቆፈሩ አዲስ ታሪክ የኢትዮጵያን እስካሁን ታሪክ የሀሰት ትርክት አድርገው የእነሱን ታሪክ በመጻፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጧል፡፡

በአማራ እና ደቡብ ማህበረሰብ ላይ የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነገ ላለመደገሙ ዋስትና የለንም ብሏል፡፡

በአለማችን በርካታ አስመሳይ አሸባሪዎች የእስልምናን ሀይማኖት ተገን በማድረግ የፈጸሙትን አገራትን የማፈራረስ ስራ ኢትዮጵያ ውስጥም እየገባ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡

በዚህ የውጥረት ጊዜም በሃሰት ሀይማኖታዊ ጥቃት ለማስመሰል ከመሞከር ውጭ ኢትዮጵያዊነትን የሚጠላ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ሌላውም ብሄርና ሙስሊም እና ክርስቲያን እንደሌለና ኢትዮጵያዊነት ከማንም በላይ ነው ሲል አብራርቷል፡፡