አባይ ሚዲያ ዜና- ህዳር 19፣2012

በመቀሌ አዉራ ጎዳኖች ላይ የተጀመረዉ ዘመቻ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንደሚዘልቅም አስተባባሪዎቹ አስታዉቀዋል።

የዘመቻዉ ዓላማ በከተማይቱ የሚገኙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ፆታዊ ጥቃት ሥለሚያደርሰዉ ማሕበራዊ፣ ስነልቦናዊና ምጣኔ ሐብታዊ ቀዉስ ተገንዝበዉ፣ ጥቃቱን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት እንዲተባበሩ ለማበረታታት ነዉ ተብሏል።

ዘመቻዉ የፆታ ጥቃትን ለመከላከል ባለፈዉ ሰኞ የተደረገዉ ዓለም አቀፍ ዘመቻ አካል መሆኑም ተነግሯል።

አስተባባሪዎቹ እንደገለጹት በዘመቻዉ በተለይ ወጣቶች ሥለጥቃቱ የተሻለ ንቃትና ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ልዩ ትኩረት ይሰጣል።