አባይ ሚዲያ ዜና- ህዳር 19፣2012

የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያዎች ሳተላይቶች በአግባቡ ተልዕኳቸውን እንዲፈጽሙ የሚቆጣጠሩ እና የተፈለገውን መረጃ ለመቀበል የሚያገለግሉ ሲሆን ያለ ሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያዎች ግንባታ የሳተላይቶች መምጠቅ ብቻውን ጥቅም የለውም።

ኢትዮጵያ የሳተላይት መረጃ ፍላጎቷን በከፍተኛ ወጪ የምታገኝ ሲሆን ፤ ይህንን በከፍተኛ የዉጭ ምንዛሬ ለግዢ የሚወጣ የሃገር ሃብት ለማዳን እና አልፎ ተርፎም በሃገር ዉስጥና በአጎራባች ሃገራት ለሚገኙ ተጠቃሚዎች የመረጃ አገልግሎቱን በመሸጥ ገቢ ማስገኘት የሚያስችል ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የእንጦጦን የሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ ጣቢያ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡

ቴሌኮሙኒኬሽን ፣ የመሬትና የህዋ ምልከታ ፣ የከተማ ልማት ፣ ዓለማቀፍ የተፈጥሮ ሃብትን መቆጣጠር፣ አደጋን መከላከል ፣ የካርታ ሥራ ፣ ግብርና ፣ የደን ልማት ፣ ሜትሮሎጂ እና ጂፒኤስ ከብዙዎቹ የሳተላይት ቴክኖሎጂ ትግበራዎች ጥቂቶቹ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡