አባይ ሚዲያ ዜና- ህዳር 19፣2012

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔራት እና ርእሳነ መንግሥታት 13ኛውን መደበኛ ስብሰባ እያደረጉ ነው።

በስብሰባው መክፈቻ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እንደተናገሩት አባል ሀገራቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀውስ አያያዝና ግጭቶችን በማስቀረት ያስገኟቸውን ለውጦች አሥምረውባቸዋል።

በተጨማሪም፣ አባል ሀገራቱ በቀጣናው ሰላም እንዲሰፍንና ልማት እንዲጠናከር የሚያደርጉትን ጥረት በስኬትነት አንሥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም አባል ሀገራት ኢትዮጵያ ተቋሙን ለበርካታ ዓመታት እንድትመራ አመኔታ ማሳደራቸውን አድንቀዋል።