አባይ ሚዲያ ዜና- ህዳር 19፣2012

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በትላንትናው እለት በሰጡት መግለጫ የብልፅግና ፓርቲ ቄሮና ፋኖ ላደረጉት ትግል የተግባር ማስታወሻ ያቆማል ማለታቸውን ተከትሎ የታሪክ መምህሩ አቶ ታዬ ቦጋለ ከአባይ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ትግል ተደርጓል ለዚህ ደግሞ መሰረታዊ ምክንያት የነበረው በደልና መገፋት ነው ብለዋል፡፡

መምህር ታዬ የቄሮና ፋኖ ትግል ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት እየተቀጣጠለ መምጣቱንም አንስተዋል፡፡

ለውጡ የተለያዩ ወጣቶች እንቅስቃሴ አስተዋፅኦ መሆኑን ያነሱት አቶ ታዬ በሀገራችን ለወጣቶች ተብሎ የቆመ ሀውልት ባይኖርም አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ሀውልት አቆማለው ማለቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

ሁልጊዜ ሀውልት ሲቆም ደጋፊም ተቃዋሚም አለው ያሉት አቶ ታዬ ለወጣቶቹ ሀውልት ቢቆምላቸው ሊቀየም የሚችለው ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ታዬ የበፊቱ ሲሉ የገለጹት ቄሮና ፋኖ የታገሉት ለሁሉም ህዝብ እኩልነት፣ ነፃነትና ፍትህ ያሉ ሲሆን በሌላ በኩል በለውጡ ከተሰሩ ስህተቶች መሳሪያ የያዘ ሀይል ከነመሳሪያው ወደ መሀል ሀገር መግባቱ ነው ብለዋል፡፡