አባይ ሚዲያ ዜና -ህዳር 20፣2012

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የሀገሪቱ መሪ ለመሆን ከአንድ መቶ አርባ በላይ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚገኙ ሲሆን በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ ያሉት ግን አርስ በእርስ በየጊዜው ራሳቸውን ከሌላ የፖለቲካ ድርጅት ጋር የመዋሀድና የማቀናጀት ጊዜ ላይ ስለሚገኙ እስካሁን በምርጫ ቦርድ በኩል በውል አልታወቁም፡፡

ይህም ለምርጫ በቀሩት ጥቂት ወራት ዉስጥ ተደራጅተው በምርጫ ቦርድ ለመመዝገብና ፓርቲ ለመሆን እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ ቡድኖችን ሳይጨምር ነው፡፡

የህግ ባለሙያዎች በበኩላቸው የምርጫ አስፈጻሚዎችን ስልጠና፣ የምርጫ ጣቢያዎች ዕድሳትና የደህንነት ሁኔታን ጨምሮ ምርጫ ቦርድ የጀመራቸው ስራዎች ከበቂ በታች እንደሆኑ ይገልጻሉ፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የምርጫ ሂደቱን በተገቢው መንገድ ለማከናወን ዝግጅቴት እያጠናቀኩ ነው ቢልም ከህግ ባለሙያዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች የምርጫ ቅስቀሳ ጊዜውን በተመለከተ ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛል፡፡

የኢህአፓ ሊቀመንበር ቆንጅት ብርሀኑ እንደተናገሩት በመጀመሪያ መንግስት የሀገሪቱን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ በማስፈን የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ መፈጠር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በበኩላቸው በየደረጃው ያሉ የምርጫ አስፈጻሚዎች እንዳልተመረጡ ጠቅሰው የምርጫ ቦርድ በተገቢው ሁኔታ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንዳልሆነ ጠቁመዋል፡፡

የኢፌድሪ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በበኩላቸው ምርጫው በተያዘለት ጊዜ ይካሄዳል ብለዋል ፡፡

ምንም እንኳን የፖለቲካ ፓርቲዎች በወጣው የምርጫ አዋጅ ዙሪያ ከስምምነት ባይደርሱም፡፡