አባይ ሚዲያ ዜና -ህዳር 20፣2012

በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ “መደመርን እንደ ፍልስፍና አላይም፤ የኢሕአዴግንም ውሕደት አላምንበትም” ማለታቸው አሳዛኝ እንደሆነ አስታወቁ።

አቶ ለማ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል በሰጡት ቃለ ምልልስ “ከመጀመሪያው ጀምሮ የፓርቲዎችን መዋሃድ በተመለከተ የማላምንበት መሆኑን ለሥራ አስፈጻሚውና ለሁሉም በስፋት ገልጫለሁ። መዋሃዱ ትክክል አይደለም፤ ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም። ወቅቱ አይደለም” ማለታቸውን በአባይ ማለዳ መዘገባችን ይታወቃል።

አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎም በበኩላቸው አቶ ለማ ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ያላቸውን ልዩነቶች እንደሰሙበት ወቅት አዝነው እንደማያውቁ በቲዊተርና ፌስቡክ ገጾቻቸው ላይ አስፍረዋል።