አባይ ሚዲያ ህዳር 22፣2012

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የልዑክ በአሜሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በመከላከያ ሚኒስትሩ የተመራው ልኡኩ በዛሬው እለት ዋሽንግተን ዲ.ሲ መግባቱንም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።

ጉብኝቱም የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑንም አምባሳደር ፍጹም ገልፀዋል ሲል የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው።

አቶ ለማ መገርሳ በቪኦኤ ቀርበው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ODP) ፈርሷል፤ የእርሶ የፖለቲካ ተሳትፎ ዕጣፈንታ ምን ይሆን ተብለው ሲጠየቁ “ከዚህ ድርጅት ውጣልን ብለው እስካልወሰኑ ልዩነቴን ይዤ እሟገታለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ቅራኔ ያላቸው፣ የሚከራከሩ ብዙ አሉ። ከሆነልን እናስተካክላለን፤ ካልሆነ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ተመካክረን የሚበጀንን እናደርጋለን።” ማለታቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡