አባይ ሚዲያ ዜና – ህዳር 23፣2012

ለዘመናት የቆየውን አብዮታዊ ዴሞክራሲና የህወሓት አገዛዝ በመጣል ከፍተኛ መስዋትነት የከፈሉት አቶ ለማ መገርሳ አሁን ላይ የተደረገውን የውህደት ሀሳብ በመቃወም በፓርቲ ደረጃ ህወሓት ሲቃወም በግለሰብ ደረጃ ብቸኛ ሆነዋል ፡፡

ውህደቱ አሁን ጊዜው አይደለም የሚሉት አቶ ለማ መጀመሪያ መመለስ ያለባቸው ህዝባዊ ጥያቄዎች መቅደም አለባቸው ይላሉ፡፡

የኢዜማ አመራር አባል የሆኑት ዳንኤል ሺበሺ በበኩላቸው አቶ ለማ የወሰኑትን ውሳኔ በተመለከተ እንዲህ ይገልጻሉ፡፡

አቶ ዳንኤል ጨምረውም ለዘመናት ስንታገልለት የነበረው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ውድቀት እውን ሲሆን ዛሬ ላይ አቶ ለማ ሀሳብ መቀየራቸው እንደ ክህደት ይቆጠራል ብለዋል፡፡

አቶ ለማ መገርሳ እስካሁን ተቃውሟቸውን ይግለጹ እንጅ ወደ ፊት ሊያደርጉ ስላሰቡት ነገር በግልጽ የተናገሩት ነገር የለም፡፡

አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ በበኩሉ ከዶቼ ቬሌ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የአቶ ለማ መገርሳ ሀገራዊ ለውጡ ላይ ያደረገው አበርክቶ ከፍተኛ እንደሆነና ጥያቄ ማንሳት ተገቢነት ያለው እንደሆነ አብራርቷል፡፡