አባይ ሚዲያ ዜና -ህዳር 26፣2012

በአለም አቀፍ ደረጃ ከወጡና የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ከሆኑት ውስጥ ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው እንዲሁም በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 9 ላይ ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የኢትዮጵያ ህግ አካል ይሆናሉ ይላል፡፡

ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው አብዛኞቹ ህጎች በአሁኑ ሰዓት እየተጣሱ እንደሚገኙ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ አቶ ዳዲሞስ ሀይሌ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ከፍተኛ ተስፋ ቢደረግም የሰብዓዊ መብት ጥሰትን መቅረፍ እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡

ህገ መንግስት የሚያዝዘውን የታሳሪዎችና ተጠርጣሪዎች መብቶች በተመለከተ ትልቅ የህግ ክፍተት እየታዬ እንደሆነ የህግ መምህሩ አቶ ዳዲሞስ ይገልጻሉ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ማክበርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነታቸውን ቢገልጹም አገባባቸው ላይ እንዳሳዩን ግን አሁን ላይ ተግባራዊ እየተደረገ እንዳልሆነ ገልጸው አሁንም ያለንን ጊዜ በመጠቀም የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለማስከበር ከፍተኛ ትኩረት መደረግ እንዳለበት አብራርተዋል፡፡