አባይ ሚዲያ ዜና – ህዳር 26፣2012
ከ25 ሺ በላይ የኢትዮጵያን ባህልና ትውፊት የሚገልፁ የብራና መፅሐፍት እና መሰል ቅርሶችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን የብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፅሐፍት ኤጀንሲ አስታወቋል፡፡
የብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፅሐፍት ኤጀንሲ መረጃዎችን በማሰባሰብ እና በማደራጀት ለጥናት እና ምርምር በማዋል ታሪክን፣ ባህልን፣ ወግን እና ፍልስፍናን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
በ2011 ዓ.ም ከሀንጋሪ መንግሥት እና ከኢምባሲው ጋር በመተባበር ከ20 ሺ በላይ የኢትዮጵያን ባህልና ትውፊት የሚናገር የተቀረፀ ድምፅ፣ ፎቶግራፎች እና መሰል ማስረጃዎች ገቢ መሆናቸውም ታውቋል፡፡
በ2012 ዓ.ም ከጀርመን መንግሥትና ኤምባሲ ጋር በመተባበር ከ25 ሺ በላይ የሀገሪቱ የብራና መፅሐፍት እና መሰል የታሪክ ሀብቶችን ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ በማሰባሰብ ገቢ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡
አሁንም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የታሪክ ማስረጃዎችን ለማስመለስ የብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፅሐፍት ኤጀንሲ ከኢንባሲዎች ጋር መስማማት እንዲቻል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡