አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 1፣2012

ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ አምሃ መኮንን የዘንድሮውን የፈረንሳይ-ጀርመን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማት አሸንፏል።

ጠበቃ አምሃ መኮንን በኢትዮጵያ በነበረው አስቸጋሪ ወቅት እና ጊዜያት ሁሉ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት እና ለሲቪል ነጻነቶች መከበር ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው ሽልማት የተበረከተለት።

ሽልማቱን የጀርመንና የፈረንሳይ አምባሳደሮች ያበረከቱለት ሲሆን ፥ በስነ ስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ እና የሙያ ባልደረቦቹ በመገኘት ከፍተኛ አድናቆታቸውን ገልጸውለታል።

የፈረንሣይ-ጀርመን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማት በየዓመቱ ታህሳስ 10 እ.ኤ.አ የሚከበረውን የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአለም ዙሪያ ለ15 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሚሰጥ ነው።

አቶ አምሃ መኮንን ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት እንደተናገሩት  ይህ ሽልማት በኢትዮጵያ ለነፃነትነ እና ለዴሞክራሲያዊ ትግል ሲታገሉ ለነበሩ እና ዋጋ ለከፈሉ ሁሉ የተሰጠ እውቅና ነው ብለዋል።