አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 2፣2012 ዓ.ም

ሰብአዊ መብት ተከራካሪ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ  በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ  ብርካታ ኢትዮጵያውያንን ሰብስቦ ባነጋገረበት እና በስብሰባው ላይ የቀረበውን ሪዞሉይሽን እና ጉዳዮን ከግብ ለማድረስ ለህዝብ እና የምሁራን እና ባለሙያዎችን ተሳትፎ ለማድረግ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ጥሪውን  ተከትሎ የተቁዋቅዋመውን ኮሚቴ ማክሰኞ ህዳር 10 , 2019 ዓም  ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለበርካታ አመታት በአሜሪካን ኮንግረንስ እና በእስቴት ዲፓርትመንት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ተከራካሪ እና እንዲሁም HR 128 ሪዞልዮሽን ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩት እና ሌሎችም ባሉበት በዋሽንግተን ዲሲስቴት ዲፓርትመንት  በመገኘት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠሪንን አነጋግረዋል ፡፡

በቀጣይም ወደ ኮንግረንስ እንደሚሄዱና ራሱን ቄሮ ብሎ የሚጠራውን ቡድን ለመክሰስ አስፈላጊውን መረጃ እየተሰበሰበ እንደሆነ አባይ ሚዲያ ያነጋገራቸው አቶ መስፍን መኮንን አስታውቀዋል፡፡ ኮሚቴው በቀጣይ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለዓለም ለማሳየትና በተባበሩት መንግስታት አግባብነት ያለው ፍትህ ለማግኘት አስፈላጊ መረጃዎች እየተሰበሰቡ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡