አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 7፣ 2012

የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በሳንሆዜ- ካሊፎርኒያ ከሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ጋር በክልሉ ልማት፣ ኢንቨስትመንት እና በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ድጋፍ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ምክክር ላይ ንግግር ያደረጉት የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር አዱኛ ወርቁ እንዳሉት ‹‹ከጩኸታችን እንቀንስና የተግባር ሰው እንሁን፤ ከዚህ ያደረሰንን ወገናችንን ዋጋም እንክፈል፤ ምን ሰራችሁ? ከማለታችን በፊት ምን ሰራን? ብለን እንጠይቅ፡፡››

“የአማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ መልዕክት በተካሄደው የሳንሆዜው ምክክር የአማራ ተወላጆች እና የኢትዮጵያ ወዳጅ አሜሪካውያን ለክልሉ ሕዝብ ሕይወት መሻሻል በጋራ ለመሥራት ቃል የገቡበት፤ በተግባር እያገዙ ያሉትም ልምድ በማካፈል ለሌሎች ቁጭት የፈጠሩበት እንደነበርም ተገልጧል፡፡