አባይ ሚዲያ ዜና – ታህሳስ 11፣ 2012

በአዲስ አበባ ከቅርቡ ጊዜ ወዲህ እየተበራከተ የመጣውን ዝርፊያ የከተማዋን ነዋሪ አላስወጣ አላስገባ ያለ ይመስላል።

በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ፖለስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋስካ ፋንታ ነዋሪዎች ለሚያነሱት የደሀንነት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

እንደ ኮማንደር ፋሲካ ስርቆቱን የሚፈጽሙት ከማረሚያ ቤት የእርማት ጊዜያቸውን አጠናቀው ከወጡ በኋላ ከአዲስ በወንጀል ተግባር ላይ ከተሰማሩ አካላት ጋር በመቀላቀል ነው ሲሉ ገልጸው በተጨማሪም ከተለያዩ ቦታ አዲስ አበባን እንደተለየ የገንዘብ ምንጭ በመቁጠር የሚመጡ አካላት መበራከታቸውንና የመጡበት አላማ አልሳካ ሲል ወደ ወንጀል ተግባር ይሰማራሉም ብለዋል።

ኮማንደር ፋሲካም ህብረተሰቡ ወንጀል በተፈፀመበት አቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሲያመለክት አያገባንም ይሄ የኛ ቀጠና አይደለም የሚል የፖሊስ አባላትን ኮምሽኑ እንደማይፈልግና ህብረተሰቡም ይህ ችግር ሲያጋጥመው በ 991 እና በ 0111-11-01-11 በደወል ጥቆማ መስጠትና እንዲጠየቁ ማድረግ ይቻላል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።