አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 13፣2012

አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት በአስተዳራዊ ስርዓት በተለይም እንደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታና አዳዲስ ሀሳቦችና የፓርቲ ሪፎርሞች በሚካሄዱበት ወቅት የሀሳብ ልዩነቶች ሊኖሩ ቢችሉም የሀሳብ ልዩነት በራሱ ችግር እንዳልሆነ ገልጸው ትልቁ ጉዳይ ይህን የሀሳብ ልዩነት እንዴት ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንፈታዋለን የሚለው ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

አቶ አዲሱ በቅርቡ የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ ለመገናኛ ብዙሃን በመደመር ፍልስፍና እንዲሁም በፓርቲው ውህደት እንደማይስማሙ የገለጹትን ጠቅሰው ይህንን ጉዳይ በኦሮሞ ባህልና ስርዓት መሰረት የቀድሞ የኦዲፒ የስራ አመራሮች ሌሎችም ኃላፊዎች በተገኙበት የበሰለ ውይይት በማድረግና የነበሩ ልዩነቶችን በማጥበብ ከዚህ በኃላም አንድነትን አጠናክሮ አብሮ ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል፡፡

አቶ አዲሱ አክለውም ፓርቲያቸው በዲሞክራሲ ባህል እና በኦሮሞ ባህልና ስርዓት የውስጥ ችግሩን ለመፍታትና ህብረተሰቡ ያለውን ጥያቄ ሁሉ ለመፍታት የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

አቶ ለማ መገርሳ በመደመር ፍልስፍናና በፓርቲዎች ውህደት ላይ የነበረቸውን ልዩነት አጥብበው የህዝቡን ትግል ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሻገር መስማማታቸው ይታወቃል፡፡

አቶ ለማ መገርሳ ከዚህ ቀደም በመደመር ፍልስፍናና በፓርቲዎች ውህደት ላይ ያላቸውን ልዩነት በኦሮሞ ባህል መሰረት ስምምነት ከተደረገ በኋላ ልዩነታቸውን አጥበው ከዚህ በኋላ በጠንካራ አንድነት በጋራ በመስራት የህዝቡን ድል ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከስምምነትም ተደርሷል፡፡

ይህ ስምምነት የተደረሰው የቀድሞ የኦዲፒ ስራ አስፈጻሚዎችና ነባር አመራሮች በጋራ ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

ፓርቲው የዴሞክራሲ ስርዓትንና በኦሮሞ ባህል መሰረት ውስጣዊ ችግሩን እና የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ጠንክሮ እንደሚሰራ ማስታወቁን ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡