አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 13፣2012

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተስፋዬ  እንደተናገሩት በጥቃቱ የተጠረጠሩ እስካሁን ድረስ 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ማህበረሰቡ ጥፋተኞችን እየጠቆመ በመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።

በፖሊስ የተያዙት ተጠርጣሪዎችም እንደተያዙበት ቅደም ተከተል ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መደረጉንም ዋና ኢንስፔክተሩ ጨምረው ገልፀዋል።

በሞጣ ከተማ ሁኔታዎች መረጋጋታቸውን የተናገሩት ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ፤ በከተማዋም ያለው ጥበቃም መጠናከሩን ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶች፣ የመንግሥት ቢሮዎች ተከፍተዋል በማለት ምናልባት የተቃጠሉ ሱቆች አካባቢ ያሉት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወደ መደበኛው ሕይወቱ ተመልሷል ሲሉ አረጋግጠዋል።

“በማኅበራዊ ሚዲያ የሚመላለሱ መረጃዎችን አይተዋቸው እንደነበር ነገር ግን ምንም በጽሁፍም ሆነ በቃል ተደራጅቶ የቀረበ ጥቆማና መረጃ አልነበረም” ሲሉ ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተናግረዋል።