አባይ ሚዲያ ዜና – ታህሳስ 15፣2012

በሩዋንዳ የሚገኘው የሀገሪቷ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ RTV ሁለት የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ድራማዎችን በትርጉም ለማስተላለፍ ከድራማው ባለቤቶች ጋር መስማማቱ ተገልጧል፡፡

ሩዋንዳ በቴሌቪዥን ለማሳየት ያሰበቻቸው ሁለት ተከታታይ የኢትዮጵያ ድራማዎች ‘ሰው ለሰው’ እና ‘ዘመን’ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

ድራማዎቹ በሩዋንዳ የቴሌቪዥን ጣቢያ በትርጉም የሚተላለፉ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ከድራማው ባለቤቶች ጋር ከስምምነት መደረሱን ምንጮች ነግረውናል፡፡

ተከታታይ ድራማዎቹ በሩዋንዳ ቴሌቪዥን መተላለፋቸው የዘርፉን ኢንዱስትሪ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ ነውም ተብሎለታል፡፡