አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 19፣2012

ሊገባደድ ጥቂት ቀናት ብቻ በቀሩት የፈረንጆቹ 2019 አሜሪኳ በታሪኳ እጅግ ከፍተኛ የሚባል የጅምላ ግድያ ማስተናገዷ ተገልጧል።

አሶሺየትድ ፕረስ፣ ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ እና ኖርዝ ኢስተርን ዩኒቨርሲቲ በትብብር ባጠናቀሩት መረጃ መሰረት በዓመቱ 41 ክስተቶች የተመዘገቡ ሲሆን በጥቃቶቹም 211 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

አንድ ጥቃት የጀምላ ግድያ ነው ተብሎ የሚፈረጀው ከጥቃት ፈጻሚው በተጨማሪ አራት ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ነው።

በአሜሪካ በሚጠናቀቀው ዓመት ለበርካቶች ሞት ምክንያት ከሆኑት የጅምላ ግድያዎች መካከል በወርሀ ግንቦት ቨርጂኒያ ቢች 12 ሰዎች የተገደሉበትና ነሀሴ ላይ ደግሞ በኤል ፓሶ 22 ሰዎች የሞቱበት የሚጠቀሱ ናቸው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ።