አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 21፣2012

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከሰሞኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች በአዳማ ከተማ የሚገኘው የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እንደተዘጋ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው ሲል አስታውቋል።

የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንዳስታወቁት በፓርቲው ላይ ከመንግሥት ወገን ጫናዎች መኖራቸውን ጠቅሰው በሌሎች ድርጅቶች ላይ የማይጠየቀው ነገር በእኛ ላይ እየተጠየቀ ነው ሲሉም ጨምረው ገልጸዋል።

ከከተማ አስተዳደሩ መንግሥት የማያውቀው የኪራይ ውል ነው ያላችሁ የሚል ጥያቄ እንደቀረበባቸው እና ይህንም ለመፍታት አስተዳደራዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል ስተል አዲስ ማለዳ ዘግባለች።