አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 21፣2012

ለዘመናት ይኖሩበት ከነበረው የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ ተነስተው ቁራቁር በተባለው አካባቢ የሰፈሩ የመልሶ ማስፈር ተሳታፊዎች ቦታው ውሃ አዘል በመሆኑ የሰሩት ቤት እየፈረሰ ለችግር መጋለጣቸውን ገለፁ፡፡

በመልሶ ማስፈር የተነሱ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ቅሬታ ቢያቀርቡም የችግሩ ምንጭ በጥናት ባለመረጋገጡ መፍትሄ መስጠት አለመቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ከ11 በላይ ግለሰቦች የቤቱ ውሃ ልክ፣ ሊሾ የሆነው ወለልና ግድግዳው ከመሰነጣጠቅ አልፎ ወደ ታች እየሰጠመ በመምጣቱ ከነቤተሰባቸው ስጋት ላይ መውደቃቸውን የተናገሩ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩና የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል ።