አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 21፣2012

ብራዚል ፌስቡክን የከሰሰችው በአገሪቱ የሚገኙ 443 ሺህ የፌስቡክ ደንበኞችን ያለፍቃዳቸው ምስጥራዊ መረጃዎችን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ በመስጠቱ ነው ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ተጠቃሚዎች ለስነ ልቦና ሰርቬ በሚል ያለፍቃዳቸው የተለያዩ መረጃዎች እንደሚሰበሰቡ የገለፀው የብራዚል ፍትህ ሚኒስትር ድርጊቱ ህገ ወጥና ከግሎባል ካምብሪጅ ትንተና ቅሌት ግንኙነት ሊኖረው ይችላል ብሏል፡፡

ፌስቡክ የስነ-ልቦናዊ ሰርቬው በሚል የተዘጋጀው አፕልኬሽን አማካኝነት ከተጣቃሚች ያለፍቃድ መረጃዎችን በመሰበሰሰብ ለኢንግሊዙ ካምብፕሪጅ ትንተና ድርጅት አሳልፍ እንደሚሰጥም መረጃው አመላክቷል፡፡

ፌስቡክ በብራዚል ዜጎች ላይ ሌላ ጉዳት ማድረስ አለማድረሱን ተጫማሪ ምርመራ እያተደረገ መሆኑን የብራዚል ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡

ፌስቡክ እ.ኤ.አ በ2018 ብቻ ከ87 ሚሊዮን ደንበኞች የተለያዩ መረጃዎች ለካምብሪጅ አናሊትካ አሳልፍ መስጠቱ ይታወሳል፡፡