አባይ ሚዲያ ዜና – ታህሳስ 25፣2012

በመሃል አዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ የሚገነባው የአሚባራ መንደር ግንባታ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ፣ የኢፌዴሪ የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት ሚኒስቴር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ፣ የአፋር ተወላጆችና ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሩ በአፋር ባለሃብቶችና በከተማ አስተዳደሩ በጋራ የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል።

መንደሩ በ50 ሺህ ካሬሜትር መሬት ላይ የሚገነባ ነው ተብሏል።

የመኖሪያ መንደሩ በውስጡ ከ450 በላይ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ጨምሮ የገበያ ማዕከላት፣ ሆቴል፣ ተመራጭ የመዝናኛና የንግድ ማዕከል፣ ኣረንጓዴ ስፍራዎች እና የአፋር ባህል ማዕከልን ያካተተ ነው።