አባይ ሚዲያ ዜና – ታህሳስ 27፣2012

በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አራት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡

እነዚህም አረና ትግራይ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ትዴፓ)፣ ባይቶና እና ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ (ሳወት) ሲሆኑ ከእነዚህ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ባለፉት ሁለት ቀናት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡

ፓርቲው በጉባኤው ወቅትም አቶ ሃይሉ ጎደፋይን የፓርቲው ሊቀ-መንበር አድርጎ የመረጠ ሲሆን አቶ አሉላ ሃይሉን ደግሞ ምክትል ሊቀ-መንበር አድርጎ መርጧል፡፡

ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ባለፉት ሁለት ቀናት ባካሄደው ጉባኤው ፖለቲካዊ ፕሮግራሞቹንና የፓርቲውን ስትራቴጂ አፅድቋል፡፡

ሳወት የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት እንዲሻሻል ከሚጠይቁ ፓርቲዎች መካከልም አንዱ ነው፡፡