አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 30፣2012 ዓ.ም

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ ዐዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፌዴራል የዳኝነት አስተዳደርና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ ዐዋጅን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡c