አባይ ሚዲያ ዜና- ታህሳስ 30፣2012 ዓ.ም

የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን ለመዝረፍና ሆን ብሎ ኬብል ለመቁረጥና አደጋ ለማድረስ በሚፈልጉ ወንጀለኞች ምክንያት በመላ ሀገሪቱ በ 6 ወራት ውስጥ 8 የተቋሙ ጥበቃዎች ህይወታቸው ሊያልፍ እንደቻለ በተቋሙ ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ፍሬህይወት ተገልጿል።

ነገሩ ወደ ተደራጀ የቡድን ወንጀል እየተሸጋገረ እንደሆነ የሚያሳይ ነውም ተብሏል።

በአዲስ አበባ ብቻ በ6 ወራት ውስጥ 119 አደጋዎች የደረሱ ሲሆን 97 በመቶው ሆን ተብለው የደረሱ የኬብል ቆረጣና የስርቆት አደጋዎች ናቸው።

የወንጀል ህጉ ሆን ብሎ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሰ ከ6 ወራት እስከ 5 አመት እስር እንደሚጠብቀው ይደነግጋል።