አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 1፣2012

እስካሁን በሃገሪቱ ፌደራሊዝም ተተግብሯል የሚባለው ፍፁም እውነትነት እንደሌለው እና ይህንንም የሚያራግቡ አካላት ስለፌደራሊዝም ግንዛቤው እንደሌላቸው የሚያሳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ፡፡

ስለፌደራሊዝም ያለን አመለካከት አዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልልና አካባቢዎች ያሉትን ሕዝቦች የሚመለከት ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ በአንድ አካባቢ የሚኖር ግለሰብ ግብር እስከከፈለ ድረስ ከአካባቢው ፖለቲካዊ ተሳትፎ ውጪ የሚሆንበት ፌደራሊዝም የለም ሲሉ በመግለፅ የሚመረጠው መንግሥት የሚተዳደረው ፤ ሕዝብ በከፈለው ግብር ከሆነ ሁሉም ግብር የከፈለ ሰው በዛ መንግሥት ላይ ኃላፊነት እና መብት አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በየአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የመረጠው አካል ከየትም ይምጣ ከየት የአካባቢው ሕዝብ እስከመረጠው ድረስ የመምራት ዲሞክራሲያዊ መብቱ ሊነካ አይገባም ያሉት ፕሮፌሰሩ የተመረጠው ግለሰብም የመረጠውን ህዝብ ያለአድሎ የማስተዳደር ግዴታም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡