አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 1፣2012

የቀድሞ ጤና ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት እና ከሀላፊነት በፍቃዳቸው የለቀቁት ዶ/ር አሚር አማን፤ በአሜሪካዊው ባለሀብት ዋረን ቡፌት ከ56 አመት በፊት የተመሰረተውና በሴቶች ወሊድና ፅንስ ክትትል በዓለም ዙሪያ ላይ ያለትርፍ በሚሰራው ሱዛን ቶምፕሰን ቡፌት ፋውንዴሽን ውስጥ ከፍተኛ አማካሪ ሆነው ስለመሾማቸው መረጃዎች እየወጡ ይገኛል።

ዶ/ር አሚር በከፍተኛ አማካሪነት ያገለግሉበታል የተባለው ሱዛን ቶምፕሰን ቡፌት ፋውንዴሽን ዋና ቢሮ አሜሪካ ኔቤሪስካ ግዛት ኦማሃ ከተማ ውስጥ እንደሚገኝ ተገልጧል።