አባይ ሚዲያ ዜና -ጥር 1፣2012

የዶ/ር ደብረፅዮን የህግ አማካሪ ‹‹መገፋት እና በደል እየደረሰብኝ›› ነው በሚል ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ገለጹ፡፡

የትግራይ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር የሕግ አማካሪ አቶ ዘርአይ ወልደሰንበት ለክልሉ ፕሬዝዳንት ባስገቡት የመልቀቂያ ደብዳቤ ላይ በትግራይ ክልል ተመድበው በሚሰሩበት የኃላፊነት ስፍራ ላይ እጅግ እልህ አስጨራሽ እና እንግዳ በሆነ የስራ ሁኔታ ውስጥ ማለፋቸውን ጠቁመው በማይሻሻል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ መቀጠል ከዚህ በኋላ ትርፉ ቀን ከቀን ንዴት ነው ያሉ ሲሆን በመሆኑም አማካሪው ከጥር 1/2012ዓ.ም ጀምሮ በአስገዳጅ ሁኔታ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡