አባይ ሚዲያ ዜና- ጥር 4፣2012

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ሊቀ-መንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ሀገራችንን በመሰረታዊነት ወደ ዴሞክራሲያዊነት የሚያሻግር ለውጥ የለም ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ለውጡ ውጥረት ነግሶባታል የሚሉት ዶክተር ደሳለኝ ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸውና ያለ ምንም ህጋዊ ማረጋገጫ ለእስር የተዳረጉበትና ትንሽ ግለሰቦች በሚያወሩት መረጃ እየተመራች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ችግሮች በየአቅጣጫው ተበራክተዋል የሚሉት ዶክተር ደሳለኝ በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለውን የመብት ረገጣ ፓርቲያቸው አጥብቆ እንደሚታገል አስታውቀው በአለም ላይ ማንም መንግስት አንድን ህዝብ በእስር ቤት ውስጥ አድርጎ በዘላቂነት የመግዛት አቅም ስለሌለው የአማራን ህዝብ እስር አያንበረክከውም ብለዋል፡፡

ከሰኔ አስራ አምስቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በሰጡት አስተያየት የሃገሪቱ የደህንነት ተቋም ከፍተኛ ክፍተት እንደሆነ ገልጸው ይህንን አሳፋሪ የሆነ የግድያ ወንጀል የሀገሪቱ የደህንነት ተቋም ቀድሞ መረጃ ሊኖረውና ችግሩ ከመከሰቱ በፊት እርምጃ ሊወስድ ይገባ ነበር ብለዋል፡፡