አባይ ሚዲያ ዜና- ጥር 4፣2012

አቶ ኃይለማርም ደሣለኝ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና አቶ ደመቀ መኮንን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነበረከት ስምኦን መዝገብ ላይ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው።

የተከሳሽ ጠበቃ፤ መጥሪያ ለአቶ ደመቀ መኮንን እና ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው መሰጠቱን ገልጸው አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝን ማግኘት ባለመቻላቸው መጥሪያ መስጠት አለመቻላቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

በፋክስ በደረሰው መረጃ መሠረት አቶ ደመቀ እና አቶ ገዱ በሥራ ምክንያት መቅረብ አለመቻላቸውን መግለጻቸውን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

አንድ ሌላ ምስክርም በዛሬው ችሎት ላይ ሳይቀርቡ ቀርተዋል።