አባይ ሚዲያ ዜና ጥር 5፣2012

በምዕራብ ኦሮምያ አራቱም ወለጋ ዞኖች የኢንተርኔትና ስልክ መቋረጡ በህገ-መንግሥቱ የተደነገገውን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የሚጋፋ ከመሆኑ በተጨማሪ ከቴሌኮሙኒኬሽን ዐዋጅ ጋርም የሚጣረስ ነው ሲሉ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ምሁራን ተናግረዋል።

የሀገርን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል የፀጥታ ሁኔታ ሲፈጠር አንዳንድ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ቢደረግም በአሁኑ ደረጃ ግን ለዚያ የሚያጋልጥ ችግር አልተፈጠረም ይላሉ ምሁራኑ፡፡

ምዕራብ ኦሮሚያን ብቻ ነጥሎ የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጥ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ነው የሚሉት ምሁራኑ ሁለንተናዊ ኪሳራውም ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡